Welcome, my Uniques
➜ My Uniques ዛሬም በ Ethio Unique Tutorial Class አዲስ Course አብረን እንጀምራለን i forget to say how is everything i think all things are good welcome back by Civic Course በድንብ አደረገን እንማማራለን ስዎች የምን መፍዘዝ ነው ነቃ ደንገጥ በሉ እንጂ።
ይህ Course እንደ Highschool አይደለም! እውነት ለመናገር በውስጡ አዲስ ነገሮች ጨምሯል ስለዚህ Be carefully 🤨 ደግሞ እንደዚህ ስላችሁ Honest review ለመሰጠት ነው እሺ but with Ethio Unique A+ Must ነው።
እሺ ስለ Course U ከዚህ በፊት እንደተናገራኩት ነው። ደረጃው ከፍ ማለቱ እንጂ ምንም የሚያስፈራ አዲስ ነገር የለውም፤ አብዛኛው ሀሳብ ከዚህ በፊት የምታውቁትና የተማራችሁት ነው። ያው ግን ጥቂት አዳዲስ የተጨመሩ ሀሳቦች አሉ፤ ቢሆንም ይህ ምርጥ እና ልዩ! Tutorial ከእናንተ ጋር ነው። ስለዚህ ወደ ዛሬው Class እንገባ እሺ Uniquely we will cover it so don't worry i am here to teach you my students.
1.1. Chapter Introduction
📝 Civics and Ethics
➜ My Students? Say My teacher ይህ ምዕራፍ 📖 እንደ ዜግነት ትምህርት (civic education)፣ ዜጋ (citizen)፣ ዜግነት በተጨማሪም፣ በዜግነትና በስነ-ምግባር መካከል ያለው አንድነት፣ የዜግነትና ስነ-ምግባር ትምህርት ግቦች እና የመልካም ዜጋ ብቃቶች/ባህሪያት የዚህ ምዕራፍ ዋና በጥልቀት የምንመለከታቸው ሀሳብ ናቸው።
ስለዚህ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ አንድ መልካም ዜጋ በህብረተሰብ ውስጥ ምን አይነት ብቃትና መልካም ስነ-ምግባር ሊኖረው እንደሚገባ በጥልቀት እንመለከታለን አው ከ እናንተ መካከልም እኮ መልካም ስነ-ምግባር የሌለው አለ አይደል ለምሳሌ Nati with beti እንደሚሉት 😭 የ Tik tok ስዎች እና የ Live ተሳዳቢዎች ማለት ነው ምን እሱ ብቻ Freshman ሆኖ ስለ ትምህርት የማይጨነቁ በ postive side የማያስብ እኮ አሉ እዚ Tutorial Class ውስጥ ግን የሉም አውቄ ነው እኮ ቢኖሩም ወደ መልካም ስነ-ምግባር እንመልሳቸዋለን እሺ በቃ ወደ ትምህርታችን እንመለስ።
1.2. Chapter Objectives
ይህ ለእናንተ ትቸዋለሁ module ተመልከቱት 👀
1.3. Defining Civics, Ethics, Morality
Human beings are social animals, which means people naturally need to live and interact with other people. We cannot live completely alone. Human beings need principles and values because they live together in society. Respecting these values helps to build a peaceful society and lead a prosperous life.
➜ My students ይሄ ሀሳብ መቼም አልገባኝም የሚል የለም። ሰው ማህበራዊ ፍጡር ስለሆነ ብቻውን መኖር አይችልም። ከቤተሰባችን፣ ከጎረቤቶቻችንና ከጓደኞቻችን ጋር አብረን ነው የምንኖረው። ነገር ግን አብሮ ለመኖር ምን ያስፈልጋል ብላችሁ ታስባላችሁ? ከሌሎች ሰዎች ጋር በሰላም ለመኖር እንደ ክብር፣ ታማኝነት፣ ኃላፊነት፣ ትብብር እና ፍትሕ ያሉ መሠረታዊ እሴቶችንና መርሆችን ማክበር ያስፈልጋል።
🤓 ምሳሌ (1) Nati የፈለገውን ብቻ የሚያደርግ ከሆነ፣ የሌላውን ሀሳብና መብት የማያከብር ከሆነ የህይወት ጊዜ በሙሉ ከሁሉም ሰዎች ጋር ችግር ውስጥ ሲገባ ነው ጊዜውን የሚያቃጥለው።
🤓 ምሳሌ (2) በኳስ ጨዋታ ላይ ሁሉም ተጫዋች የራሱን ህግ ብቻ ቢከተል ምን እንደሚፈጠር አስቡት? አደጋ ይበዛል፤ ስለሆነም፣ በሰላም አብሮ ለመጫወት የኳስ ጨዋታ ህግ ያስፈልጋል ማለት ነው።
➜ ሁላችንም ልናከብራቸው የሚገቡ መሠረታዊ መርሆዎችና እሴቶች አሉን። እነዚህን እሴቶች ማወቅና መተግበር ደግሞ የዜግነት ትምህርት (Civic Education) ዋና ትኩረት ነው!
John Stuart Mill
📝 According to John Stuart Mill (1972), a society can achieve continuous progress and lasting peace only if it actively fosters the personal qualities of its members and nurtures good citizens.
My uniques John Stuart Mill የሚባለው ታዋቂ ፈላስፋ የገለጸውን ሀሳብ ተመልከቱ። "አንድ ማህበረሰብ ወይም ሀገር እድገትና ለውጥ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም ሊኖረው የሚችለው፣ እያንዳንዱ ወይም ሁሉም የማህበረሰቡን አባላት መልካም ስብዕና እና ለመማር Ready ሲሆኑ ወይም እውቀት ማሳደግ ሲችል ነው" ይለናል።
Aristotle
📖 Aristotle (1955) emphasized that the citizens of a nation should be educated in alignment with the principles and structure of their state's constitution.
➜ የጥንቱ ታላቅ ፈላስፋ እና ሁሉም ነገር ላይ አለው ማለት የሚወደው (Aristotle) ደግሞ ሌላ በጣም ወሳኝ ሀሳብ ያክላል፤ "የአንድ ሀገር ዜጎች ትምህርት የሚሰጣቸው ከሀገሪቱ ህገ-መንግስት (Constitution) ጋር አብሮ በሚሄድ መልኩ መሆን አለበት" ይላል።
አሁን እዚህ ጋር Chemistry እና English ትምህርት ከ Constitution ጋር አብሮ መሄድ አለበት ማለት አይደለም እሱ እንደተነገረው ከሆነ Critical thinking እንደሚባለው የምትማሩት ትምህርት ከ Construction aptitude የወጣ መሆን የለበትም ማለት ነው ስለዚህ አንድ ሀገር የምትገነባው በተማሩ ዜጎች ነው እነዚህ ዜጎች ደግሞ ትምህርታቸው ህገመንግስት የሚጣረስ መሆን የለበትም ማለት ነው።
Good citizens & civic education
📖 Accordingly, creating a good citizen has been the prior concern of many States, including Ethiopia.
➜ My Uniques ይሄ ማለት የተለያዩ የዓለም ሀገራት ትልቅ ትኩረት የሚሰጡትና ዋነኛ ዓላማ የሚያደርጉት "ጥሩ ዜጋን" (Good Citizen) ማፍራት ነው! ነው እንጂ Tik Tok ላይ ተቀምጦ የሚሰዳደብ አይደለም 🤭 ምክንያቱም ሀገርን የሚያቆሟትና የሚያሳድጓት ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ ህግ የሚያከብሩና ለህዝባቸው የሚያስቡ ዜጎች ናቸው።
Civic Education has different names in different countries because each country may have its own political system, culture, and educational goals. However, the main purpose is almost the same: to prepare people to become good, responsible, active, and democratic citizens. Civic Education teaches citizens about their rights, which are the things they are allowed to have or do, and their responsibilities, which are the duties they are expected to perform. It also teaches important values and principles, such as respect, equality, justice, responsibility, and cooperation. In addition, students learn about the constitution, which contains the basic rules and principles of a country. Civic Education also encourages people to participate in society, meaning they should not only know their rights and responsibilities but also actively contribute to their community and country.
እስካሁን የተመለከትነውን እናጠቃል
Civic Education በተለያዩ አገሮች የተለያዩ ስሞች ያሉት ሲሆን ምክንያቱም እያንዳንዱ አገር የራሱ የፖለቲካ ሥርዓት፣ ባህል እና የትምህርት ዓላማ ሊኖረው ስለሚችል ነው። ሆኖም ዋና ዓላማው በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው፤ ማለትም ጥሩ፣ ኃላፊነት የሚሰማው፣ ንቁ እና ዴሞክራሲያዊ ዜጋ ማፍራት ነው።
Civic Education ዜጎች ስላሏቸው መብቶች እና ኃላፊነቶች እንዲያውቁ ያስተምራል። መብት ማለት እንደ ዜጋ የሚፈቀድልን ወይም የሚገባን ነገር ሲሆን፣ ኃላፊነት ማለት ደግሞ እንደ ዜጋ መወጣት የሚገባን ግዴታ ማለት ነው።
በተጨማሪም ክብር፣ እኩልነት፣ ፍትሕ፣ ኃላፊነት እና ትብብር ያሉ እሴቶችንና መርሆችን ያስተምራል። እንዲሁም ህገ-መንግስትን ማለትም የአገርን መሠረታዊ ህጎችና መርሆች እንዲረዱ ያግዛል። በመጨረሻም ሰዎች መብታቸውንና ኃላፊነታቸውን ብቻ እንዲያውቁ ሳይሆን፣ በማህበረሰብና በአገር ጉዳዮች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያበረታታል።
መልካም እስካሁን መቼም የገባችሁ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ እንቀጥል …
ለመመዝገብ
የዚህን Tutorial ሙሉ ክፍል ለማግኘት አሁኑኑ ይመዝገቡ ለመመዝገብ @EthioUnitutorial_bot መጠቀም አለቀ።
መልካም ጊዜ 🙌 ሁሉም with Ethio Unique anything is possible 🥰
Register · ለመመዝገብ